Mols.gov.et

በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ ሚና አበርክቷል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

April 14, 2025
በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ ሚና አበርክቷል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ ሚና ማበርከቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የ100 ቀናትና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ የዘጠኝ ወራት አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሰጡት ማብራሪያ፥ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም የኢኮኖሚ መስኮች የሀገርን ዕድገት የሚያስቀጥሉ ትልልቅ ስኬቶችን አስመዝግባለች ብለዋል። የሥራ ዕድል ፈጠራ ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር ተሳስሮ የሚታይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ÷ በዚህም በሁሉም መስክ የተመዘገበው ስኬት ለዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል ነው ያሉት። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እየተሰራባቸው በሚገኙት የግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድንና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች ትርጉም ያለው ስኬት እንደተመዘገበ ተናግረዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል መቀየር ያስቻለ እሳቤን በመተግበር ረጅም ርቀትን መጓዝ የሚያስችል ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለም አንስተዋል። በበጀት ዓመቱ 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተቀምጦ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውሰዋል። በዚህም በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዕቅዱን 86 በመቶ በማሳካት ለ3 ነጥብ 4 ሚሊየን ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ጠቅሰዋል። የግብርና፣ አገልግሎትና ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ መስኮች በቅደም ተከተል ከፍተኛውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ድርሻ መያዛቸውንም አስረድተዋል። በውጭ ሀገራት የሥራ ስምሪት ቀልጣፋ፣ ሕጋዊና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓትን በመዘርጋት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 344 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና በርካታ ዜጎች የዲጂታል ክህሎታቸውን በማሳደግ በዓለም የሥራ ገበያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ፈጠሯል ብለዋል። ከትላልቅ የውጭ ኩባንያዎች የሥራ ትዕዛዝ በመቀበል እስካሁን 45ሺህ ኢትዮጵያውያን በርቀት ሥራ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። በሥራ ዕድል ፈጠራ ሂደቱ የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የሙያዊ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነወ። ሚያዝያ 6፤ 2017
tigTIG
Scroll to Top