በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው፡፡
October 28, 2024
በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የ100 ቀናት የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራር እና ሠራተኞች ተገኝተዋል፡፡
በዚህም ክብርት ሚኒስትር ዓበይት ሀገራዊ ክንውኖች እና ተግባራዊ የተደረገውን የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬቶች እና ነባራዊ ሁኔታ አዝማሚያዎች ላይ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብብራሪያም ሰጥተዋል፡፡
መድረኩ መላው ሠራተኛ በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረው እና ድርሻውን እንዲወጣ የተዘጋጀ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር እንደ ሀገር የተደረገው የተሟላ ሀገራዊ ሪፎርም የምንፈልገውን ውጤት እያመጣ ነው፡፡
በተሟላ መልኩ መተግበር በጀመረው ሪፎርም እየመጣ ያለውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲቪል ሰርቫንቱ የማይተካ ሚና አለው ብለዋል፡፡
እንደ ሀገር የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙም በተሰጠ ቆራጥ አመራር መሰረተ ሰፊ የሆነ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መደረጉን ጠቁመው ጊዜንና ጉልበትን እሴት በሚያክሉ፣ ሰላምን በሚያጸኑ ተግባራት ላይ ማዋል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የሰው ሀይል ምርታማነት ለማሳደግም ሲቪል ሰርቪሱ ሙስንናን የሚጠየፍ፣ ግዜውንና ጉልበቱን በአግባቡ የሚጠቀም አድርጎ መገንባት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የመድረኩ አመራርና ሠራተኞች በበኩላቸው በትልልቅ ሀገራዊ ጉዳች ላይ ሠራተኛውን ባለቤት ማድረግ መጀመሩ መጀመሩ አዲስ ባህልና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ የተደረገው ውይይትም ጊዜውን የጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
አፈፃፀሙ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን የጠቆሙት የመድረኩ ተሳታፊዎች እንደ ዘርፍ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጅ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡