Mols.gov.et

በበጀት ዓመቱ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላትን በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን ሥራ ይሰራል፡፡

October 24, 2024
በበጀት ዓመቱ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላትን በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን ሥራ ይሰራል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ ከሰዓት በፊት የደቡብ ምዕራብ እና የትግራይ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የክልሎቹ ሁሉም ከፍተኛና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱ የክልሎቹ የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአሠሪና እና ሠራተኛ ግንኙነት እና የተቋም ግንባታ የሦስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የተያዘው በጀት ዓመት በዘርፉ በተተገበሩ የሪፎርም ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን በማጽናትና በማላቅ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የምናሳድግበት ነው፡፡ ለዚህ ግብ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለየ የድጋፍና የክትትል ሥራዎችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ በየደረጃው መሰል የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡ በዚህ ዓመት በትኩረት ከተያዙ ሥራዎች ዋነኛው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከላት መሆናቸውን ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ማዕከላቱ የሚሰጡት አገልግሎት ቀልጣፋ፣ ግልጽ፤ ፍትሃዊና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡ የሚሰጡት ሰርተፊኬት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ማዕከላቱ ራሳቸው አውቅና ማግኘት እንደሚኖርባቸውም አንስተዋል፡፡ በዚህም ማዕከለቱ በቴክኖሎጂና በአሠራር የማዘመን እንዲሁም የሰው ሃይሉን አቅም የማሳደግ ሥራ በትኩረት እንደሚሠራ ክብርት ሚኒስትር ጨምረው ገልፀዋል፡፡
tigTIG
Scroll to Top