3ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ዌልዲንግ ፌዴሬሽን ኮንፈረስ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ በዊልዲንግ የአፍሪካ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ምክክሮች፣ የዌልዲንግ ውድድሮች የልምድ ልውውጦች እና የመስክ ጉብኝቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
መድረኩ “አፍሪካን ማብቃት ለክልላዊ ውህደት እና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የብየዳ አቅምን ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በአድዋ ሙዚየም እየተካሄደ ይገኛል።