የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤
October 28, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓት ግንባታ (system thinking) ላይ ተወያዩ፤
በሪፎርም አስተሳሰብ ውስጥ የተወለደው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዳዲስ እሳቤዎችንና አሠራሮችን በመቅረፅ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ከእነዚህ አዳዲስ አሰራሮች መካከል ተናባቢ የሆነ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) በሚኒስትር መ/ቤቱ ለማስጀመር የሚያስችል የፐብሊክ ሰርቪስ ላብ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ነው ፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአስተሳሰብ ሥርዓትን (system thinking) ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ለካውንስል አባላቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ወጥ የሆነ እሳቤን ቀርፆ በየደረጃው የጋራ መግባባትን ለመፍጠር የሚስችል ሥራ ሲሰራ ቆይቷል።
የዲጂታል አማራጮችን ጭምር በመጠቀም ዘርፉን ተናባቢ በሆነ መልኩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
የሥራና ክህሎት የተሰጠውን ተልዕኮ በሚመጥን መልኩ ከጫፍ እስከ ጫፍ ተናባቢ የሆነ ሥርዓትን ለመገንባት እያንዳንዱ አመራር ኃላፊነቱን በትኩረት መወጣት እንደሚኖሩበትም በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡