Mols.gov.et

በድጅታል ክህሎት የሰለጠኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሴት ሰልጣኞች ተመረቁ

October 18, 2024
በድጅታል ክህሎት የሰለጠኑ ከአንድ ሺህ በላይ ሴት ሰልጣኞች ተመረቁ፡፡ ስቴም ፓወር(STEM power) ከፊንላንድ ኤምባሲ እና ከ IBM SkillsBuild ጋር በመተባበር በጅታል ክህሎት ላይ ላለፉት ሶስት ወራት በኦንላየን ያሰለጠናቸው አንድ ሺህ ስልሳ ዘጠኝ(1069) ሴት ሰልጣኞች አስመርቋል፡፡ ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ የሚገኘው ስቴም ፓወር ትጋት ፕሮጀክት በሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙ ያሰለጠናቸው እነዚህ ሴት ሰልጣኞቹ በሶፍትዌር ዲቨሎፕንት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI)፣ በሳይበር ሰኩሪቲ እና በዳታ ቤዝ የመሳሰሉ ድጅታል ክህሎቶች ላይ ስልጠናቸውን እንደተከታተሉ ተጠቁሟል፡፡ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ፤ የድጅታል ክህሎት ዘርፍ እጅግ ውስብስብ፣ተገማች ያልሆነ፣ተለዋዋጭ፣ አሻሚ እና ድንበር የለሽ ቢሆንም ክህሎት እና እውቀትን ባልተቋረጠ መልኩ ማሻሻል ከተቻለ በሠፊ ዕድሎች የተሞላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዘርፉ ዕድሎች ለመጠቀም ልዩ ትጋት በሚጠይቀው በዚህ ስልጠና አልፈው ለተመረቁ ሴት ተመራቂዎችም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ ተመራቂዎችም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባመቻቸው በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ተመዝግበው በሪሞት ጀብስ፣ በውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት እና በተለያዩ አማራጮች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ የመሆን ሰፊ ዕድል እንዳላቸው አማላክተዋል፡፡
somSOM
Scroll to Top