Mols.gov.et

በዘርፉ ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም በቀጠናው፣ በሀጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ…

February 29, 2024
በዘርፉ ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም በቀጠናው፣ በሀጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር ይጠይቃል፡፡ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ላለፉት አራት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው 5ኛው የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም ዛሬ ተጠናቋል፡፡ “የመደበኛ ፍልሰት ትሩፋቶች ለወጣቶች የሥራ ዕድል፣ ለክህሎት ልማት እና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው በዚህ መድረክ በቀጠናው መደበኛ ፍልሰትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የክህሎት ልማት እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ያለው ፋይዳ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተለይተዋል፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት፣ አፍሪካ የወጣቶች አህጉር እንደመሀኗ ያላትን የስነ-ህዝብ አወቃቀር በአግባቡ ለመጠቀም ፎረሙ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሀጉር ሥራ አጥነትና ህገ-ወጥ ፍልሰት አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የኢትዮጵያ ፎረሙን በሊቀመንበርነት በመራችበቻቸው ያለፉት ሁለት ዓመታት በዘርፉ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲመዘገቡ የበኩሏን ጥረት አድርጋለች፡፡ በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም በቀጠናው፣ በሀጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ያሉ የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ አጋርነትን መፍጠር ይጠይቃል ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ ቀልጣፋ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህጋዊ የሠራተኞች ፍልሰት አስተዳደር ስርዓት የዘረጋች መሆኑን ጠቁመው የግሉ ሴክተርን አቅም በመጠቀም የወጣቶች የሥራ ዕድል እና ክህሎት ልማቱን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ በመድረኩ ኢትዮጵያ ለቀጣይ ሁለት አመታት የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚኒስትሮች የፍልሰት ጉዳዮች ፎረም ሊቀመንበርነትን ለኡጋንዳ አስረክባለች።
somSOM
Scroll to Top