Mols.gov.et

ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት…

January 10, 2024
“ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት ትጉህ እና ትሁት የሆነ አመራር ያስፈልጋል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በውጤታማ አመራር ሰጪነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ለተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች ተሰጥቷል፡፡ ሥልጠናውን የሰጡት በአሜሪካን ሀገር በውጤታማ አመራር ሰጪነት (effective leadership) ላይ ከፍተኛ ልምድና ተሞክሮ ባላቸው አሰልጣኞች ነው፡፡ በሥልጠና መድረኩ ላይ የተሳተፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስተር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ህዝብንና ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርግ ተቋም ለመገንባት ትጉህ እና ትሁት የሆነ አመራር ያስፈልጋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ከመሆኑም ባሻገር አገልግሎት የሚሰጡ አካላትንም የሚያሰለጥን በመሆኑ በየደረጃው ለዚህ ምላሽ መስጠት የሚችል አመራር ያስፈልጋል ብለዋል።
somSOM
Scroll to Top