Mols.gov.et

የአፍሪካ ወጣቶችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ የዲጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር

July 7, 2025
የአፍሪካ ወጣቶችን ህይወት የተሻለ ለማድረግ የዲጅታል መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሴክተሪያት እና ከኤትሬድ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመድረኩ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ የዘርፉ ምሁራን፣ ተመራማሪዎችና ሥራ ፈጠሪዎች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ፎረሙ ከአፍሪካ የትስስር ሳምንት ጋር በመቀናጀት የመላው አፍሪካውያን ኩራት በሆነው በአድዋ የድል በዓል መታሰቢያ ሙዚየም መካሄዱ እጅግ ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል ብለዋል፡፡ አፍሪካ የበርካታ ወጣቶች አህጉር መሆኗን ሸክም ሳይሆን ተጨማሪ አቅም መሆኑን ጠቁመው ወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በድጅታል ፋይናንስ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ዘመናዊ ግብርና ላይ በትኩረት እየሰራች ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ እንደ አህጉር ለድጅታል የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና እሴት ሰንሰለትን ለተከተለ የግብርና ልማት ትኩረት በመስጠት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ መደላድል መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፤ ፎረሙ የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ እንቅስቃሴ አሁን ካለው የዓለም አውድ ጋር አሰናስሎ መምራት በሚቻልበት ሁኔታ ምክክር ይካሄዳል ብለዋል፡፡ በዋናነት ይህ መርሃ ግብር የግብርና እሴት ሰንሰለት እና የድጅታልና የፋይናንስ አካታችነት ላይ ሃገራቶች ተሞክሮ የሚለዋወጡበት እና ኢትዮጵያም በዘርፉ ያከናወነችውን ተሞክሮ የምታቀርብበት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም የወጣቶች ተጠቃሚት ላይ ያተኮሩ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል ብለዋል፡፡ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም #AJCF2025, #Jobs4Africa, #AfCFTA, #DigitalInclusion, #YouthEmployment
oroORO
Scroll to Top