ፕሮጀክቶችን ወጥና ግልጽ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል ሲስተም መልማቱ ተገለፀ፡፡
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ተልዕኮዎች ለማሳካት ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በትብብር የሚተገበሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሥር የሚገኙ ፕሮጀክቶቹን ወጥና ግልፅ በሆነ መልኩ ለማስተዳደር እንዲቻል በሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ የለማው ሲስተም ላይ ገለጻ ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መከለያ በርጊቾ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ ፕሮጀክቶችን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ ለመምራትና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ይተገበራል ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል ዲጂታል የሆነ ወጥ የሆነ አሠራር መዘርጋቱ ስራዎችን ከማቀላጠፍና ግልፅነትን ከማስፈን ባለፈ የፕሮጀክቶቹን አፈፃፀም ከማላቅ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የስትራተጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም አሥራት ጠቁመዋል: