Mols.gov.et

የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሙያ ማማከርና ድጋፍ አገልግሎት መምሪያ ሰነድ ይፋ ሆነ፡፡

November 28, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር (GIZ) GmbH፣ ካሪታስ ስዊዘርላንድ እና ከሌሎችም የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር ያዘጋጀው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሙያ ማማከርና ድጋፍ አገልግሎት መምሪያ ይፋ ተደርጓል፡፡ መምሪያው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ አስፈፃሚ፣ ባለድርሻና አጋር አካላት በተገኙበት ይፋ የተደረገ የተደረገ ሲሆን ለሁሉም ክልሎችና ለሁለቱ ከተማ አስተዳድሮች የማስረከብ ሥራ ተከናውኗል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ ዶ/ር ተሾመ ለማ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ መምሪያው ሚኒስቴሩ በክህሎት ዘርፍ እየሰራው የሚገኘውን ሥራ የሚደግፍ፣ የክህሎት ሥልጠናውን የሚያሻሽል ብሎም የሰልጣኞችን እና ምሩቃን በመደበኛ ትምህርት ከሚያገኙት እውቀት በተጨማሪ ውስጣዊ አቅማቸውን አውጥተው እንዲጠቀሙ እና የሙያ የማማከር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡ መምሪያው ወጣቶች የወደፊት የሥራ ዕድላቸው በሚያገኙት መረጃ ተመስርተው እንዲወስኑ የሚያግዝ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደየ ክልሎችና እና ከተማ አስተዳደሮች ነባራዊ ሁኔታ ውጤታማ የሚያደርግ አደረጃጀት በመፍጠር በፍጥነት ወደ ሥራ እንዲሚገባ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top