Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ጋር በትብብር መስራት…

July 30, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ፤ ተወዳዳሪ እና ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ የክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ የመፍጠር ሥራ ውጤታማ እንዲሆን የአመራር ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም ከአመራር ልማት ሥራ ባለፈ አካዳሚው የኢንተርፕረነርሺፕ ባህል ለመገንባት ከሥርዓተ ሥልጠና ቀረጻ ጀምሮ፣ ተወዳዳሪ የሆኑ፣ አምራች ዜጎችን መፍጠር የሚያስችል ምቹ አውድ እስከ መፍጠር ድረስ የሚከናወኑ ተግባራትን በማላቅ ረገድ ያለው ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብረሃ በበኩላቸው፤ ስምምነቱ በዋናነት የአመራር ልማት፣ የሥራና ክህሎት ልህቀት ሽልማት፣ የሥራ ባህል ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ግንባታ እና የጥናትና ምርምር ሥራዎችን አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top