Mols.gov.et

ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ አገራት ለተውጣጡ የእስልምና እምነት ተከታይ ሠልጣኞች የኢፍጣር መርሐግብር አካሄደ።

March 25, 2025
ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ አገራት ለተውጣጡ የእስልምና እምነት ተከታይ ሠልጣኞች የኢፍጣር መርሐግብር አካሄደ። የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ አገራት መጥተው በኢንስቲትዩቱ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ላሉ የእስልምና እምነት ተከታይ ሠልጣዮች የአፍጥር መርሐግብር አካሂዷል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ረመዳን የወንድማማችነት፣ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ ወር መሆኑን ገልጸው ይህ የኢፍጣር መርሐግብር የተዘጋጀው ይህንንኑ በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል። ኢንስቲትዩቱ በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቀጠናው አገራት ዜጎችን ነጻ የስልጠና እድል እየሰጠ እያሰለጠነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ የአፍጥር ፕሮግራሙ ተካፋይ ከሆኑ መካከል የሶማሌላንድ እና የደቡብ ሱዳን ተማሪዎች በዚህ የአብሮነት የወንድማማችነት ወር በጋራ አፍጠር ስለተዘጋጀላቸው ምስጋናቸውን አቅርዋል፡፡ ኢትዮጵያ ባህል ሐይማኖት ብዝሐነት ያላት አገር መሆኗን ያነሱት ሰልጣኞት ይህንን የመሰለ ፕሮግራም መዘጋጀቱ እንዳስደነቃቸውም ጨምረው ገልጸዋል፡፡ በአፍጥር ሥነስርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
oroORO
Scroll to Top