Mols.gov.et

ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ …

August 9, 2024
ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ከመጣንበት መንገድ የተለየ ፈጣንና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅብናል ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ እየተገበራቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ፡፡ የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎትሚኒስቴር ለዜጎች ሰፊና ውጤታማ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ ከሚገኙ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በሀገራችን ያለውን ሰፊ ፍላጎት የሚመጥን ስራ መስራት ይጠይቃል ያሉት ክብርት ሚኒስትር ሰፋፊ፣ ዘላቂና ጥራት ያላቸው የሥራ ዕድሎችን በብዛት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከመጣንበት መንገድ የተለየ ፈጣንና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top