Mols.gov.et

Dereje Geremew

News

ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን የፈጠነ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን የፈጠነ እንዲሆን የሚያደርግ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃው ለሚያካሂደው የማህበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት ለአዲስ አበባ አስተዳደር የአመቻችነት የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡
በሥልጠና ማስጀመሪያው መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ ማኅበረሰብ-አቀፍ የምርታማነት ውይይት የሥራ ባህላችንን በማሳደግ፣ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን አሟጦ በመጠቀም የማህበረሰባችንን እሴት የማከልና የመፍጠር አቅምን ለማውጣት ያለመ ነው፡፡
ይህም ዜጎች አካባቢያቸውን እና የልማት ፀጋዎቻቸውን እንዲያስተውሉ፣ በችሎታቸው እንዲተማመኑና የማድረግ አቅማቸውን ከማሳደግ ባሻገር የቤተሰብን፣ የግለሰብንና የማህበረሰብን ምርታማነት የምናሳድግበት የለውጥ መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡
ሂደቱ በየአካባው ያሉ ችግሮችን በመለየት ወደ መልካም አጋጣሚነት መቀየርን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ መነሻነት እያንዳንዱ አካባቢ ፀጋውን መሰረት ያደረገ የራሱ መለያ የሚሆን ምርት ማውጣት እንደሚጠበቅበትም አመላክተዋል፡፡
ውይይቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችን ያጠረና የፈጠነ፤ ፈጠራን ያከለና ያማከለ እንዲሆን እንደሚያደርግም ጨምረው ገልጽዋል፡፡
በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአዲስ አበባ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ በበኩላቸው፤ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠቱ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የሥራ ባህልን ለማሻሻል ያግዛል ብለዋል፡፡

Read More Âť
News

ችግር ለመፍታት፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…

ችግር ለመፍታት፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…
በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በጋራ መፍታትን፣ አፈፃፀምን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሻሻልን እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ታሳቢ በማድረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የድጋፍና ክትትል ቡድን የሚያደርገውን የመስክ ምልከታ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ቡድኑ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች ከሪፖርት ባሻገር ያሉበትን የአፈፃፀም ሁኔታ በመመልከት ችግሮችን መፍታትና አፈፃፀሙን ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
በዚህም ቡድኑ ከክልል፣ ከከተማ አስተዳድርና ከየወረዳው አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የተመረጡ የግልና የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን፣ ኢንተርፕራይዞችን፣ የገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን እና የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን በመመልከት ላይ ነው፡፡

Read More Âť
News

የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተገመገመ

የሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ተገመገመ
የተጠሪ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ተገምግሟል።
በመድረኩ የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲቲዩት፣ የቱሪዝም ኢንስቲቲዩት እና የኢንተርፕርነር ልማት ኢንስቲትዩት እንዲሁም የአምስቱ የግብርና ኮሌጆች ዕቅድ አፈፃፀም በየተቋማቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋማቱ የተሻለ አፈፃፀሞችን አልቆ ማፅናት እና ክፍተቶችን በፍጥነት ማረምና መሙላት እንደሚገባ አሳስበው ይህንንም በልዩ ዕቅድ ለመመለስና ሪፎርሙን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል::

Read More Âť
News

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን የመስክ ምልከታ እያደረገ ይገኛል

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን የመስክ ምልከታ እያደረገ ይገኛል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በሀረሪ፣ በማዕከላዊና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲሁም በሸገር ዙሪያ በመንቀሳቀስ ከየክል የሥራ ኃላፊዎቸ ጋር በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ሥራዎች ላይ ውይይት በማድረግ እስከ ታችኛው መዋቅር በመውረድ ሥራዎችን ተመልክቷል፡፡
ቡድኑ በምልከታው ከክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት እና ተቋም አቅም ግንባታ አኳያ እንደ አቅጣጫ የተቀመጡ ሥራዎችን ያሉበትን ደረጃ የመፈተሸ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡
ለአፈፃፀም ማነቆ የሆኑ ጉዳችን በመፍታት ለላቀ አፈፃፀም መደላድል መፍጠር አላማው ባደረገው በዚህ የድጋፍና ክትትል ሥራ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማቱ የየዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

Read More Âť
News

ፈጠራንና ፍጥነትን ያማከለው የሸገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተሞክሮ …

ፈጠራንና ፍጥነትን ያማከለው የሸገር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተሞክሮ …
በዘርፉ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎቻችን የዜጎችን እለታዊ ችግሮች ከመቅረፍ ባሻገር ጥሪት ማፍራት እና ሀብት መፍጠር ላይ እንዲያተኩር ተደርጓል፡፡
የሚፈጠረው የሥራ ዕድልም እሴት ሰንሰለትን፣ ፈጠራ እና ፍጥነትን ማዕከል ያደረገ እንዲሆን አቅጣጫ ተቀምጦ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የኦሮሚያ ሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮም ይህን አቅጣጫ ተግባረዊ በማድረግ በዘርፉ ተጨባጭ ሥራዎችን መሬት ላይ ማውረድ ችሏል፡፡ ለበርካታ ወጣቶችም የሥራ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል፡፡
በክልሉ የሸገር ከተማ አስተዳደር ለከተማው ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የመንግስትን በጀት ሳይጠብቅ እየሄደበት ያለው ርቀት በዘርፉ ለሌሎች ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጭምር ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ሥራ መሆኑን ሰሞኑን በከተማው የተገኘው የፌዴራል የድጋፍና ክትትል ቡድን ተመልክቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን በዘርፉ ትልቅ ፈተና ሆኖ የሚገኘውን የመስሪያና የመሸጫ ቦታ ችግር ለመቅረፍም የመስሪያና የመሸጫ የሼዶች ግንባታ እያከናወነ ይገኛል፡፡
በ21 ሄክታር ላይ ያረፈው የመጀመሪያው የግብርና ክላስተር ሼዶች ግንባታ በያዝነው በጀት ዓመት መስከረም መር የተጀመረ ነው፡፡ አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ምዕራፉ ላይ ይገኛል፡፡
300 የሚሆኑ ሼዶችን ያቀፈው ይህ ክላስተር እሴት ሰንሰለትን መሰረት ያደረገ የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲያስችል ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
በዚህም ሼዱ ከመኖ ማቀነባበሪያና የእንስሳት ጤና ኬላ ጀምሮ እሴት የሚያክሉና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን በሙሉ እንዲያቀፍ ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡
በመልካ ናኖ ክፍለ ከተማ እየተሰራ ያለው ይህ ግንባታ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ፣ የሀገር በቀል ሙያዎች ክላስተር ሼዶችን ጨምሮ የትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት ግንባታ እና የኮሊደር ልማትን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪው 2.5 ቢሊየን እንደሚጠጋ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህን ፕሮጀክት ከሌሎች ተመሳሳይ ሥራዎች ልዩ የሚያደርገው ምንም አይነት የመንግስት በጀትን ያልጠየቀና ሙሉ ለሙሉ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የሚሰራ እንዲሁም በፍጥነትና በጥራት የተገነባ መሆኑ እንደሆነም የከተማው አመራሮች ለድጋፍና ክትትል ቡደኑ ገልፀዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ የሚስተዋለውን የግብዓትና ግብይት ችግርን ለመቅረፍም ክላስተሩ የመኖ ማቀነባበሪያ እና የመሸጫ ቦታዎችም እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡
ከክላስተሩ ባለፈ በከተማው 181 በላይ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት G + 6 የገበያ ማዕከል በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ቀን ተሌት ርብርብ እያደጉ ይገኛል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገር የሥራ ባህላችንንም ጭምር እንድንቀይር እድል ፈጥሮልናል የሚሉት የከተማው አመራሮች ሥራው በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወን ሁሉም የከተማ አስተዳድሩ አመራሮች ርብርብ እያደረጉ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራው የድጋፍና ክትትል ቡድንም ከሼዱንና ከገበያ ማዕከሉን በተጨማሪ የቡራዩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን፣ የፋም ውሃ ፋብሪካን፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልን እና ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሥልጠና እየሰጠ የሚገኝውን ሀባቦ የቤት አያያዝ ማሰልጠኛ ተቋምን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሃመድ ከጉብኝቱ በኳላ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ ሚናቸው የላቀ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥልና ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ሊሰፋ ይገባል ብለዋል፡፡
ለክልሉ እና ለከተማ አስተዳደሩ አመራሮችም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰጡ ላለው ቁርጠኛ አመራርም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Read More Âť
News

ለጥንቃቄ!

ለጥንቃቄ!
ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጫት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን እየገለጽን ዜጎቻችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡

Read More Âť
News

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው…

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሚሰጠው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሀገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን አድራሻ እና ፍቃድ ያገኙበትን የመዳረሻ ሀገራት ዝርዝር ለማግኘት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ https://t.me/c/1438397174/2327

Read More Âť
News

በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ተሳትፎና ለክህሎት ልማት የሰጠች ትኩረት የዓለም አቀፉን ሚዲያ ትሉረት የሳበ ነበር፡፡

በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ተሳትፎና ለክህሎት ልማት የሰጠች ትኩረት የዓለም አቀፉን ሚዲያ ትሉረት የሳበ ነበር፡፡
በሀገረ ቻይና ቲያንጂን ከተማ የተካሄደው የቴክኒክና ሙያ ልማት ኮንፈረነስ ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች እና ዘርፉ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተሳተፉበት መድረክ ነው፡፡
በመድረኩ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ተሳታፏል፡፡
በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ይህን ተከትሎ የቻይናውን ትልቁ የሚዲያ ተቋም የሆነውን ዥንዋን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት የኢትዮጵያን ተሳተፎና ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል፡፡
ዥንዋ ኢትዮጵያ የክህሎት ልማት ሥራውን ከሀገራዊ የልማት ዕቅዶች ጋር በማዋሃድ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቷ ለመጠቀም እየተከተለች ያለችውን አቅጣጫ በሰፊው ተመልክቷል፡፡
ግሎባል ታየምስ የተሰኘው እለታዊ የቻይና ጋዜጣም የሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ መገንባቱና በመድረኩ ያደረገቸው ተሳተፎ የክህሎት ልማትን መሰረት በማድረግ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገትን ለማምጣት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረትን የሚያሳይ ነው ሲል አስነብቧል።
የሉባን ወርክሾፕ ኢትዮጵያ እና ቻይና የነበራቸውን ግንኙነት በትምህርትና ሥልጠና እና በቴክኖሎጂ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ የክህሎት ልማት የአፍሪካውያን አጀንዳ እንደሚሆንም አመላክቷል።
መቀመጫውን ሞስኮ ያደረገው የብሪክስ ቴሌቭዥን በበኩሉ ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፉ ላይ ትኩረት በመስጠት ከቻይና ጋር ስምምነት መፈረሟን በመጥቀስ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በማሳደግ ላይ መሆኗን ተመልክቷል፡፡
ቻይና ዴይሊ የሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነቸው አዲስ አበባ መገንባቱን ጠቅሶ ይህም ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ዘመኑን የዋጀ የክህሎት ልማትን እውን ለማድረግ ዓለም አቀፍ ትብብሯን አጠናክራ መቀጠሏን ተመልክቷል፡፡

Read More Âť
News

በክልሉ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በክልሉ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በጋምቤላ ክልል በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በዚህም ቡድኑ በተዘዋወረባቸው የመንግስትና የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትም ሆነ በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማረጋገጥ አንፃር ሥራ ፈላጊዎች የሚመዘገቡበት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቁመው ነገር ግን ከሚፈለገው አንፃር በቂ እንዳልሆነ ገልፀዋል።
በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቅበላ አቅማቸው ጥሩ ቢሆንም ዜጎችን ወደሥራ ከማስገባት አንፃር ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል።
ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እንደሚያከናውን ገልፀዋል።
የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሯች ባየክ በበኩላቸው በተያዘው በጀት ዓመት የክልሉን ፀጋዎች ትርጉም ባለው መንገድ በመጠቀም ብቁና ተወዳዳሪ ሥራ ፈጣሪ ዜጋን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የክልሉ ወጣቶች ባለው የአካባቢው ፀጋ ላይ እንዲደራጁ በማድረግ በተለይም በማዕድን ሀብት እና በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተፈጠረውን መነቃቃት በመጠቀም በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።
በፌዴራል መንግስት እየተሰጠ ያለው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውንም አቶ ሯች ተናግረዋል።
የክትትል ቡድኑ እየተሰጠ ካለው የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ የአቅም ክፍተቶችን በመለየት በስልጠና ለመሙላት እያደረገ ያለው ጥረትም የሚመሰገን መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Read More Âť
News

\\በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን…

በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመስክ ምልከታ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና እንዱስትሪ ግንኙነት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት በማድረግ በሁለት ዞኖች ላይ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
በጋሞ እና በኮንሶ ዞን በተካሄደው የመስክ ምልከታ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እና ኢንዱስትሪዎች ታተዋል፡፡
ለድጋፍና ክትትል ሥራው የመጣውን ቡድን የክልሉና የዞኖቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

Read More Âť
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top