Mols.gov.et

Admin Mols

News

ፀጋን ማወቅ፣ ተጠቃሚነትን ማላቅ!

ፀጋን ማወቅ፣ ተጠቃሚነትን ማላቅ!
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር በጀመርናቸው የትብብር ሥራዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡
የትብብር ትኩረታችን ያሉ ክልላዊ የልማት ፀጋዎችን በአግባቡ በመጠቀም በክህሎትና በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በቀጣይም የክልሉን የመልማት አቅም በሂደቱ የእውቀትና ክህሎት እንዲሁም ቴክኖሎጂ ሽግግር እውን ለማድረግና ሰፊና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ በዝርዝር መክረናል።
ይበልጥ አካታች፣ ዘላቂ፣ የኑሮ ዘዬው የተሻሻለና የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሉን አቀፍ ጥረት ለማድረግም ተግባብተናል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሊ ሀሰን ቅንጅታዊ ሥራው እንዲሳካና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰጡት ላለው ጠንካራ አመራር ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Read More »
News

ከውድድር ወደ ምርት…

ከውድድር ወደ ምርት…
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እያደረጋቸው ከሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች መካከል አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ ችግር ፈቺ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎቻቸውን በማበልፀግ ለገበያ ማብቃት አንዱ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት በ2016 በጀት ዓመት‹‹ሰመር ካምፕ›› በሚል ፕሮግራም ከመላ ሀገሪቱ የተወጣጡ ከ400 በላይ ተሳታፊዎች በማሰባሰብ ከ83 በላይ የውጭ ምርትን የሚተኩና አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች ማምረት ተችሏል።
ከእነዚህ ቴክኖሎጂዎች መካከል ዮናስና ጓደኞቹ የሰሩት ጭስ አልባ በሆነ መንገድ ከሠል የሚያከስል እና የእጽዋት መኖ ማቀነባበር የሚችል ቴክኖሎጂ ይገኝበታል።
ቴክኖሎጂው “Sumi-automated Charcoal and Animal Feed Production Machine” የማል ስያሜ ተሰጥቶታል።
ይህ ቴክኖሎጂ በአገራችን ቆላማ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የከርሰ ምድርን ውሃ የሚያጠፋውንና እና የእርሻ መሬትን የሚጎዳውን በሳይንሳዊ ስያሜው Prosopis Juli Flora weed በመባል የሚታወቀውን አረምን በግብዓትነት ይጠቀማል።
ከተለያየ የአገራችን አካባቢ የተሰባሰቡት ወጣት ዮናስ እና ሌሎች የሠመርካምፕ ቴክኖሎጂስቶች አልፋ ኢንጂነሪንግን የሚል ኩባንያ መስርተው ቴክኖሎጂውን በብዛት በማምረት ላይ የሚገኙ ሲሆን የቴክኖሎጂውን ፋይዳ የተረዳው የኢፌዲሪ መስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂው በስፋት እንዲመረት እያደረገ ይገኛል።
ይህ አረም ከአገራችን አልፎ የበርካታ የአፍሪካ አገራት ችግር በመሆኑ ቴክኖሎጂውን በቀጣይ ወደተለያዩ አገራት አምርተው የመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸውም የቴክኖሎጂው ባለቤቶች ገልጸዋል።

Read More »
News

ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም የመጀመሪያ ምዕራፍ አፈጻጸምን ገምግሞ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በመድረኩ በመጀመሪያ ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ለትግበራው የሚያስፈልጉ የሰነድና የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም አደረጃጀትን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ተቋማዊ ልህቀትን በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በዚህም የመጀመሪያውን ምዕራፍ በማጠናቀቅ የቀጣዩን ምዕራፍ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መደላድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን፣ ተደራሽነትንና ፍትሃዊነትን ለማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቴክኖሎጂ በሰፊው ጥቅም ላይ እንደሚውልም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማቱ ላይ በሚተገበረው የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ላይ ግልጽነት ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት በየደረጃው ሲካሂድ ቆይቷል፡፡

Read More »
News

‹‹የክህሎት ኢትዮጵያ›› ተሳታፊዎች የፈጠራ ሀሳባቸውንና ቴክኖሎጂዎቻቸውን ከተለያዩ ተቋማት ለተገኙ ባለሙያዎች የሚያቀርቡበት መርሃ ግብር ተጀምሯል።

‹‹የክህሎት ኢትዮጵያ›› ተሳታፊዎች የፈጠራ ሀሳባቸውንና ቴክኖሎጂዎቻቸውን ከተለያዩ ተቋማት ለተገኙ ባለሙያዎች የሚያቀርቡበት መርሃ ግብር ተጀምሯል።
መርሐግብሩን ያስጀመሩት የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ባስተላለፉት መልዕክት፣ በሀገራችን ብዙ አዳዲስ ነገር መፍጠር የሚችሉ ዜጎች በመኖራቸው በቁጭት የተጀመረ ነው።
በመጀመሪያው የቴክኖሎጂና የፈጠራ ሀሳብ ማበልፀጊያ መርሃ ግብር የተሳተፉ ወጣቶች ሥራዎቻቸውን ወደ ሙሉ ምርት የማሸጋገር ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
‹‹በአገራችን የክህሎት ልማት ሥራ ብዙ የተደከመበትም ቢሆንም የቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ፕሮግራሞችን እስከጀመርንበት እስካለፈው ዓመት ድረስ ተገቢውን ቅርጽ አልያዘም ነበር ብለዋል፡፡
የኢኒስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ በበኩላቸው፣ የውድድሩ ተሳታፊዎች አስቀድሞ የልል ክህሎት(soft skill) ስልጠና እንደተሰጣቸው አመላክተዋል።
አሁን በተጀመረው መርሃ ግብር ሀሳባቸውን በአግባቡ በመሸጥ ውጤታማ ሆነው የሚያልፉ ተሳታፊዎች በቀጣይ ክህሎታቸውን የሚያሳድጉ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን አንዲወስዱ በማገዝ ወደ ምርት እስኪሸጋገሩ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ ከሁሉም የሀገሪቱ የተወጣጡ 147 የሚሆኑ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳብና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ይዘው የቀረቡ ተሳታፊዎች ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል።
መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ እና የኢንተርኘሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋራ በትብብር የሚዘጋጅ ነው።

Read More »
News

የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክርን ለአካባቢያዊ ጸጋ ልየታና ለምርታማነት

የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክርን ለአካባቢያዊ ጸጋ ልየታና ለምርታማነት
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየተገበራቸው ከሚገኙ ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎች መካከል በሥራ ባህል ላይ ለውጥ የሚያመጡና ምርታማነትን የሚያጎለብቱ የማኅበረሰብ ምክክሮችን በሁሉም ክልሎች በየደረጃው ማካሄድ አንዱ ነው፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱ በ2016 በጀት ዓመት የማኅበረሰብ ምክክር ለማካሄድ የሚያስችል ስትራቴጂ ቀርፆና ለውይይት አመቻቾች ተገቢውን ሥልጠና ሰጥቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
በዚሁ መሰረት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በአስር ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች በተካሄዱ ምክክሮች ከ2ሚሊዮን የሚልቁ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ መሆናቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የማኅበረሰብ አቀፍ ምክክር አፈፃፀም ከክልል አስተባባሪዎች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡
በተለያየ ደረጃ በተካሄዱት ምክክሮች ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማህበረሰብ ድረስ ያሉ አካባቢያዊ ፀጋዎች እየተለዩ ሲሆን እንደየአካባቢዎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ኅብረተሰቡን ምርታማ ሊያደርጉ የሚያስችሉ ዕድሎችና ተግዳሮት የሆኑ ጉዳዮች ላይ ጭምር ነዋሪዎች ውይይት እንደሚያደርጉ በመድረኩ ተብራርቷል፡፡
ተወያዮች ከሥራ ባህል ጋር ለሚስተዋሉ ችግሮች መፍትሔን ከማመላከት ባሻገር አከባቢያዊ አቅሞችን በመጠቀምና የራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ወደምርት የሚያስገቡ ፕሮጀክቶችን ወደመቅረጽ እየተሸጋገሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በቀጣይም የሥራ ባህል ግንባታና የምርታማነት የማኅበረሰብ ምክክር በተካሄዱባቸው አካባቢዎች “በአንድ ወረዳ አንድ ፕሮጀክት” በሚል መሪ ሃሳብ ከምክክር የሚመነጩ የፕሮጀክት ሀሳቦችን በማኅበረሰብ ባለቤትነት ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችሉ የፀጋ ልየታው ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል፡፡

Read More »
News

ከረዳትነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት…

ከረዳትነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት…
ወጣት አምሀ በቀለ ይባላል፡፡ ነዋሪነቱ በሐረር ከተማ ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በአንድ ግለሰብ የእንጨት ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት ውስጥ በረዳትነት በመቀጠር ነበር የሥራውን ዓለም የተቀላቀለው፡፡
ሥራ ከጀመረባት የመጀመሪያዋ ዕለት አንስቶ እያንዳንንዱ ነገር እንዴት እንደሚሰራ በትኩረት ያስተውል እንደነበር ይናገራል፡፡ ከዕለት ወደ እለትም ለሙያው ያለው ፍቅር እየጎለበተ ሄዶ በስድት ወር ቆይታ ብቻ ራሱን ችሎ የተለያዩ የእንጨት ውጤቶችን መስራት የሚችል ባለሙያ ለመሆን በቃ፡፡
ችሎታውንና ብቃቱን ያስተዋሉት ቀጣሪዎቹ የሚሰጡት ማበረታቻ የበለጠ ጉልበት ሲሆነው ፈጠራን ጭምር በማከል በሚሰራቸው ቁሳቆሶች የረኩ ደንበኞችም አድናቆትን ያጎርፉለት ጀመር፡፡
‹‹ለአምስት ዓመታት በቅጥር በቆየሁበት ጊዜ የቀሰምኩት ልምድ ክህሎቴንና እንዳዳብርና የደንበኞችን ፍላጎት እንድረዳ ዕድል የሰጠኝ ከመሆኑም በላይ የራሴን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል በራስ መተማመን አላብሶኛል ›› ይላል አምሀ፡፡
በዚህ መሰረት ቆጥቦ ባጠራቀመው ገንዘብ ላይ ከቤተሰብ ያገኘውን የፋይናንስና የመስሪያ ቦታ ድጋፍ አክሎበት የራሱን ሥራ አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
ምንም እንኳን ለአዲስ ቢዝነስ ጀማሪ በገበያው ላይ ተቀባይነትን ማግኘት ቀዳሚው ፈተና ቢሆንም አምሀ ግን ጥራት ያለውን ምርት በተመጣጣኝ ዋጋና በፍጥነት በማቅረብ የገበያ ማጣትን ተግዳሮት መሻገር እንደቻለ ይገልፃል፡፡
ሥራውን በየዕለቱ ማሳደግና በገበያ ላይ ያለው ተቀባይነት የላቀ እንዲሆን ማስቻል ዋንኛ ግቡ በመሆኑ የሚያገኘውን አብዛኛውን ትርፍ ቢዝነሱን ለማስፋፋት እንደሚያውለው ይናገራል፡፡
ኪችን ካቢኔት፣ ቁምሳጥን፣ ኮንትሮል ቡፌና የውስጥ በሮች አምሀ በጥራት የሚሰራቸውና ተለይቶ የሚታወቅባቸው ምርቶች ናቸው፡፡
‹‹የትኛውን የእንጨት ውጤት በልዩነት መስራት እንደምችል ማወቄ ምርቶቼ የበለጠ ተቀባይነት እንዲኖራቸው አድርጓል›› የሚለው ወጣት አምሀ በአካባቢው ምን አይነት ምርት በስፋት ይፈለጋል የሚለውን ለመገንዘብም ገበያውን በየጊዜው እንደሚያጠናም ይናገራል፡፡
ዘመናዊ የማምረቻ መሳሪያዎችን መጠቀም የምርትን ጥራት ለማረጋገጥ የሚስችል እንደመሆኑ አዳዲስ ማሽነሪዎችን ለማሟላት በየጊዜው ጥረት ከማድረግ ወደኋላ ብሎ አያውቅም፡፡ ከዚህም አልፎ ግን የፈጠራ ብቃቱን በመጠቀም ሥራን ሊያቀሉ የሚችሉ መሳሪያዎችን ራሱ ሰርቶ በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡
ከ2010 ጀምሮ በግል ኢንተርፕራይዝነት መመዝገቡ ደግሞ የሥራውን ውጤታማነቱ የሚያረጋግጡ መንግስታዊ ድጋፎችን ለማግኘት በር ከፍቶለታል፡፡
ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት የምርቱን ጥራት የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አግኝቷል፡፡
ሙያዊ ብቃቱን በምዘና ማረጋገጡና የፈጠራ ሥራዎቹ ሀገር አቀፍ እውቅናን ማግኘት መቻላቸውንም ይናገራል፡፡
አምሃ በአስር ሺ ብር የጀመረው ቢዝነስ ዛሬ ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላይ ደርሷል፤ ለሰባት ወጣቶችም ቋሚ የሥራ ዕድልን ፈጥሯል፡፡
ከውጭ የሚገቡ መምርቶችን በአይነትና በጥራት የሚወዳደር፣ በገበያ ላይ ሰፊ ተቀባይነት ያለው ምርት የማምረት ብሎም ኢትዮጵያዊ ምርቶችን ለዓለም ገበያ የማቅረብ ህልምን የሰነቀው አምሀ በሀረሪ ክልል በተገነባውና ለእንደእርሱ አይነት ውጤታማ ወጣቶች በተመቻቸው ምቹና ደረጃውን የጠበቀ የማምረቻ ማዕከል ውስጥ ቀን ከሌት በትጋት ይሠራል፣ አእምሮውን ፣ ልቡንና እጆቹን በማቀናጀት ውብና ድንቅ የሙያ ውጤቱን ለደንበኞቹ እያቀረበም ይገኛል፡፡

Read More »
News

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ክልል የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ክልል የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡
በመድረኩ በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘረፍ በግማሽ ዓመት አፈፃፀምና የሱፐርቪዥን ግኝቶች እንዲሁም በማህበራት ምጣኔ ማሳደግና አማካሪ ቦርድ ለማቋቋም በሚያስችለው የህግ ማዕቀፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በመድረኩ በተቀመጠው የህግ ስርዓት መሰረት የአማካሪ ቦርድ እንዲቋቋምና ወደ ሥራ ለማስገባት እንዲቻል የአሠሪና ሠረተኛ ማኀበራት መደራጀት ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል፡፡
በከልል የአሠሪና ሠራተኛ ማኀበር የመደራጀት ምጣኔ በማሻሻል የአማካሪ ቦርድ ለማቋቋም የአስፈፃሚ አካሉን አቅም ማጎልበትና በጉዳዩ ላይ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ መድረኩ መዘጋጀቱም ተጠቅሷል፡፡
የአሠሪዎችና ሠራተኞች በማህበር መደራጀት የኢንዱስትሪ ሰላምን ከማረጋገጥ ባሻገር ምርትና ምታማትን ለመጎለበት በሚኖረው ሚና እና በክልሎች የሚቋቋመው አማካሪ ቦርድ በሚኖረው ተግባርና ሃላፊነት ላይ ውይይት ይካሄዳል፡፡
በቀሪ ወራት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read More »
News

በልምድ ያገኙትን ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠቱን ማዕከሉ አስታወቀ

በልምድ ያገኙትን ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠቱን ማዕከሉ አስታወቀ
የሐረሪ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በልምድ ያገኙትን ክህሎትና ብቃት በምዘና ላረጋገጡ ባለሙያዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።
በማዕከሉ እውቅና የተሰጣቸው የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች እንደሆነም ተጠቁሟል።
የማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ በዳሳ ገመዳ በኢትዮጵያ ከመደበኛ ሥልጠና ውጪ የሙያ ባለቤት የሆኑ በርካታ ባለሙያዎች አሉ።
በልምድ የተገኙ እውቀቶችን እውቅና በመስጠት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ብልፅግና ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በልምድ የተገኘ ክህሎት በምዘና በማረጋገጥ እውቅና መስጠት የዜጎችን የራስ መተማመን ለማሳደግ እንዲሁም አካታችነትን እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም አመላክተዋል።
ማዕከሉ በክልሉ የሚኖሩ ዜጎች ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት ለማድረግ እየሰራ ነው ተብሏል::
በቀጣይም በተለያዪ ሙያዎች እውቅና የመስጠት ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት።

Read More »
News

በሀገራችን የመጀመሪያው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ሊዘጋጅ ነው።

በሀገራችን የመጀመሪያው የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ሊዘጋጅ ነው።
መዝገበ ቃላቱን የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ መሆኑ ተጠቁሟል።
ሁለቱ ተቋማት መዝገበ ቃላቱን በትብብር ለማዘጋጀት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለፁት፣ ኢንስቲትዩቱ ለረጅም ዓመታት በስልጠና ፣ በጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ለዘርፋ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን አውስተዋል።
ከመዝገበ ቃላት ዝግጅቱ ባለፈም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በቀጣይነት እንሰራለን ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ለሀገራችን ቱሪዝም ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የቱሪዝም መዝገበ ቃላት ለማጠናቀቅ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቋንቋና ባህል ልማት ኢንስቲትዩት ደይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ በበኩላቸው፣ መዝገበ ቃላቱ ለሀገራችን ቱሪዝም እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸው በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኩል ወደ 4000 የሙያ ቃላት መሰብሰቡን ተናግሯል ።

Read More »
News

በጀት ዓመቱ በክህሎት ልማት ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች የምንሰራበት ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ

በጀት ዓመቱ በክህሎት ልማት ዘርፍ ትርጉም ያለው ለውጥ የሚያመጡ ሥራዎች የምንሰራበት ነው፡፡
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ያለፉት ስድስት ወራት የክህሎት ልማት ዘርፍ ስራዎች አፈጻጸም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ( ዶ/ር) ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት እና የየክልሉ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እየተገመገመ ይገኛል፡፡
ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) መድረኩን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በጀት ዓመቱ ዘርፉን ወደ ፊት የሚያስፈነጥሩ የተለዩ ስራዎች የምንሰራበት እና የጀመርናቸው የሪፎርም ስራዎች የምናጸናበት ነው ብለዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች እየተፈጸሙ የሚገኝበት አግባብ ለማየት የድጋፍና ክትትል፣ ቨርቿል እና አስቸኳይ የገጽ ለገጽ መድረክ በመጥራት ውይይቶች መደረጋቸውን ገልጸው ይህ መድረክም ከቦታ ቦታ የሚታዩ የአፈጻጸም ልዩነቶችን ለማጥበብ፣ እቅዶቻችንን ዳግም ለማየት እና የቀሪ ስድስት የወራት የዘርፉ የርብርብ ማዕከል አጀንዳዎችን በመለየት ወደ ስራ ለመግባት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡
ዘርፉ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው የተቀመጡ አካባቢያዊ ጸጋን መነሻ ያደረገ ስልጠና መተግበር፣ የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማጠናከር፣ ቲቬት ድጅታላይዜሽን፣ የማሰልጠኛ ተቋማት የውስጥ አቅም ማጠናከር፣ የአይሶ ትግበራ፣ ጥራት ያለው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስልጠናዎች መስጠት የመሳሰሉት ስራዎች ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

Read More »
The Minister Is answering questions live in zoomClick To join the live Meeting
+
en_USEN
Scroll to Top