ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር አካባቢን በደንብ ማየትን፣ በጆሮ ብቻ ሳይሆን በልብ ማዳመጥን እና በጋራ መስራትን ይጠይቃል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ህዳር 14, 2024
ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር አካባቢን በደንብ ማየትን፣ በጆሮ ብቻ ሳይሆን በልብ ማዳመጥን እና በጋራ መስራትን ይጠይቃል።
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
‹‹ክህሎት ኢትዮጵያ ›› 2ኛው ሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።
መርሃ ግብሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌድሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢኒስቲትዩት እና ከኢንተርፕሪነርሺፕ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ የፈጠራ ውጤቶችን የማምረት ዓላማ ባለው በዚህ መድረክ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎ፣ የዘርፉ ባለድርሻና አጋር አካላት ተገኝተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ‹‹ክህሎት ኢትዮጵያ›› የቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ የዓለም ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ የሆነችውን ኢትዮጵያ ክብር የሚመልሱ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤቶች የሚፈሩበት መርሃ ግብር ነው፡፡
ኢትዮጵያ ስልጣኔን ለዓለም ያሳየች ሀገር ነች ያሉት ክብርት ሚኒስትር ይህንን ገናናነት መመለስ የሚችሉ ወጣቶች አሉን።
ይህም ብሔራዊ ቁጭት፣ ያለን የልማት ፀጋ እና የመለወጥ ፍላጎት ለመርሃ ግብሩ መጀመር ገፊ ምክንያት እንደሆነም ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር ያሉ ችግሮች ለሥራና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዕድሎች ናቸው። ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ ለመቀየር አካባቢን በደንብ ማየትን፣ በጆሮ ብቻ ሣይሆን በልብ ማዳመጥን እና በጋራ መስራትን እንደሚጠይቅም አመላክተዋል።
ይህም ብርታትን፣ ጽናትን፣ ሥራ ወዳድነትን፣ የሀገር ፍቅርን፣ የዜጎች ህይወት የመቀየር ፍላጎትን እና መሰጠትን ይልጋል ብለዋል።