Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ እና እድሳት …

ታህሳስ 16, 2023
የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ እና እድሳት ለማዘመን በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በማካተት እየተሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት እየተሰጠ የሚገኘውን የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ እና እድሳት አገልግሎት አስመልክቶ ከተለያዩ ድርጅቶች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ በአሁን ወቅት በርካታ አገልጎሎቶች እየሰጠ በሚገኘው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ውስጥ የተካተተው የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ እና እድሳት አገልግሎት፤ አጠቃቀሙ፣ መሟላት ስለሚገባቸው አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎች እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ባለሙያዎች ሰፊ ገለጻ እና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡ በመድረኩ የተገኙት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሀገር ውስጥ ሥራ ስምሪት ማስፋፍያ ዴስክ ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ፤ ለውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፍቃድ የሚሰጠው በዋናነት በኢትዮጵያውያን ሊሸፍኑ በማይችሉ ስራዎች ላይ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የተዘጋጀው በበለጸገው መረጃ ሥርዓት ላይ ድርጅቶች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ስራውን ማሳለጥ እንዲችሉ ነው ብለዋል፡፡ ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጥ የሥራ ፈቃድ ያሉብን የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ እና የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት በሚያስችል መልኩ ለማካነወኑ ድርጅቶች ህጋዊ መንገዶችን ብቻ ተከትለው ሥራቸውን እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡ በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎች ቢስተካከሉ ያሉዋቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው በባለሙያዎች እና በሥራ አስፈጻሚው ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
amAM
Scroll to Top