የተለያዩ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድርን በመጎብኘት ተወዳዳሪዎችን እያበረታቱ ይገኛል
ግንቦት 8, 2025

የተለያዩ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድርን በመጎብኘት ተወዳዳሪዎችን እያበረታቱ ይገኛል
በዚህም በምክትል ኮሚሽነር ሉባባ ጀማል የተመራው የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን አመራርና ሰራተኞች ሀገር አቀፍ የክህሎት ወድድርን ጎብኝቷል።
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ማረም፣ ማነጽ እና ተሃድሶ ልማት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ሉባባ ጀማል የተመራው የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም በስሩ የሚገኙ የሁለት ማዕከላት የተመረጡ ተሳታፊዎች
በሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድሩ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች እና ቴክኖሎጂዎችን ተዟዙረው ተመልክተዋል።
ምክትል ኮሚሽነረዋ ከጉብኝቱ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ታራሚዎችን በክህሎት ማበልጸግ የሚያስችሉ በርካታ ቴክኖሎጂዎችና የፈጠራ ውጤቶችንን መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በቀጣይ ታራሚዎችን ስራ ፈጣሪ እና አምራች ዜጋ አድርጎ ለመቅረጽ የሚያስችሉ ለተቋሙ የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎች እና የፈጠራ ውጤቶች በመለየት በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ስራዎችን ጀምረናል ብለዋል።
በቀጠለው 4ኛው የክህሎት ውድድር በርካታ የግልና የመንግስት ተቋማት አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች የቀረቡ አስገራሚ የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጎብኘታቸውን ቀጥለዋል።
ሚያዝያ 2/2017ዓ.ም የጀመረውን የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር እስከ ግንቦት 2/2017ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል።









