የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
ነሐሴ 19, 2024
የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ተግባራዊ የሚያደርጉት የአገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ አፈፃፀምን አስመልክቶ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት ከተቋማቱ የካውንስል አባላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሪፎርም ትግበራውን አስመልቶ በየዘርፉ ሲከናወኑ የነበሩ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ መልዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለፁት፣ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ዋና ዓላማ ሀገር መገንባት የሚያስችሉ ተቋማትን መፍጠር ነው፡፡
ይህን በአግባቡ በመረዳት በየደረጃው የሚገኝ አመራር በቁርጠኝነት መፈፀምና ማስፈፀም ይኖርበታል ብለዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎችን በአይሶ ስታንዳርድ እና ፐብሊክ አንተርፕረነርሺፕ የመሳሰሉ የሪፎርም መሳሪዎች ትግባራዊ እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር ይህም ለሪፎርሙ ትግበራ ምቹ መደላድል ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡
በቀጣይ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በየደረጃው ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር በዝርዝር ውይይት የሚካሄድ ይሆናል፡፡