Mols.gov.et

ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የክህሎት ልማት እና….

ታህሳስ 5, 2023
“ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የክህሎት ልማት እና ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር የተቋማችን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።” ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሃመድ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ “ወጣቶችን በማብቃት የብልጽግናን ጎዞ እናረጋግጣለን ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዳማ ከተማ የሥራ ላይ ልምምድ ያደረጉ እና የህይዎት ክህሎት ስልጠና ያገኙ ወጣቶች የእውቅና መስጫ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላለፋት 6 ወራት የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ እና የሥ ላይ ልምምዳቸውን ሲያደርጎ የቆዮ 1 ሺህ 744 ወጣቶች ዕውቅና እና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኘው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሃመድ አንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር በተባባሪነት ከሚተገብረው ፕሮጀክት መካከል “ብቃት” አንዱ ነዉ ። የዓለም ባንክ ይህንን ፕሮግራም ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር ሲዘረጋ ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የክህሎት ልማት እና ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር የተቋማችን ተልዕኮዎች መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ብለዋል፡፡ “ወጣቶችን ማዕከል ያደረገ የክህሎት ልማት እና ዘላቂ የሥራ ዕድል መፍጠር የተቋማችን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን የጠቆሙት ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ይህንን ስልጠና ከተከታተሉት መካከል ለ1737 ወጣቶች የሥራ ዕድል የተፈጠረ መሆኑ ትልቅ ዕድል ነዉ አመላክተዋል። ይህንኑ ዕድል በማስፋትም ሌሎች ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
amAM
Scroll to Top