ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተከፍቷል፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ፈጠራ በእጅጉ ያስፈልገናል፡፡ የእጅ ጥበብ ያላቸው፤ እጃቸውን፣ ልባቸውን፣ አዕምሯቸውን አስተሳስረው የሚሰሩ ሰዎች ያስፈልጉናል፡፡
ግብርናችን፣ ኢንዱስትሪያችንም ሆነ ኮንስትራክሽን ዘርፉ አልዘመነም፡፡ ብዙ ሴክተር በመፍጠር ሥራን ማቅለል የሚያስችል ሁኔታን መፍጠር የሚያስችል ሀገር ነው ያለን፡፡
ይህ ለማድረግ ግን ማንኛቸውን በአካባቢያችን ያሉ ፈተናዎች፣ ተግዳሮቶች እንዳያቆሙን በተባበረ፣ በተደመረና በተሳሰረ መልኩ ችግርን ብቻ በሚያወራ ሳይሆን መፍትሄ በሚያመጣ እሳቤ በመፍጠር ኢንዱስትሪያችንን እንድናዘምን አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡
እንበርታ፣ እንፍጠር፣ ፈተናንና ችግርን ለማለፍ መፍትሄ ላይ የምናተኩር እንሁን ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዚህ መንገድ የበለፀገች ሀገር ለመፍጠር ሁላችንም በየሙያችን የምንረባረብ እንሁን ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡