Mols.gov.et

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሥራ ድረጅት ምክትል የበላይ አካል (ILO governing body) ሆና ተመረጠች

ሰኔ 7, 2024
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሥራ ድረጅት ምክትል የበላይ አካል (ILO governing body) ሆና ተመረጠች በጄኔቫ እየተካሄደ በሚገኘው 112ኛው ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፈረንስ ላይ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ በክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የሚመራ የልዑካን ቡድን በመሳተፍ ላይ ይገኛል። ጉባዔው ዛሬ ባከሄደው የዓለም ሥራ ድረጅትን በበላይነት የሚያስተዳድሩ ምክትል አባል ሀገራት መካከል ኢተዮጵያ አንዷ ሆና ተመረጣለች፡፡ ከአፍሪካ ከተወዳደሩት ሰባት ሀገራት መካከል ሀገራችን ኢትዮጵያ ከደቡብ አፈሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ነው የተመረጠችው። ደርጅቱን በበላይነት የሚያስተዳድሩ (governing body) አባል ሀገራት የዓለም ሥራ ድረጅት (የILO) ዋና ሥራ አሰፈፃሚ አካል ሲሆን የድርጅቱን ዋና ዳይረክተር ምርጫን ጨምሮ በድርጅቱ ፖሊሲዎች፤ ፕሮገራሞችንና በጀት ላይ ለሚቀጥሉት 3 አመታት የሚወስን አካል ነው፡፡ ይህም ሀገራችን በድርጅቱ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የድርጅቱን ሥራ በቅርብ ለመከታተልና ከድርጅቱ ተገቢውን ድጋፍ ለማግኘት ካለው ፋይዳ ባለፈ የአገራችንን ተደማጭነት በመጨመር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውክልና ከፍ በማድረግ የገፅታ ግንባታችንን እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ደረጃችንን ያሳድጋል።
amAM
Scroll to Top