Mols.gov.et

አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞ

ሐምሌ 25, 2024
አዲሱ የጥቃቅንና አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ለሥራ ዕድል ፈጠራ አስቻይ ሁኔታ በመፍጠር እና የዘርፉን ችግሮች በመቅረፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል። ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሰምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅንና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ፖሊሲ ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ ፖሊሲው ለዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር እና የዜጎችን ገቢ ትርጉም ባለው መልኩ ማሳደግ የሚያስችል ነው፡፡ የዘርፉ አዲሱ እሳቤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠርና ዳቦ በልተው እንዲያድሩ ከማድረግ የዘለለ መሆኑን ጠቁመው አዲሱ ፖሊሲ ይህንን ታሳቢ አድርጎ የተቀረጸ ነው ብለዋል። በመድረኩ ፖሊሲውን ተከትለው የተዘጋጁ የሥራ ፈጠራ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የኢንተርኘራይዞች የኢኮኖሚ ቀውስ ጊዜ ምላሽ መስጫ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ እና ከፍተኛ የማደግ አቅም ያላቸው ኢንተርኘራይዞች ማበረታቻ ስርዓት ሰነዶች ለውይይት ቀርበው ተጨማሪ ግብዓት የሚሰባሰብበት ይሆናል፡፡
amAM
Scroll to Top