Mols.gov.et

ነገን ዛሬ እንትከል!

ሐምሌ 17, 2023
የሥራና ክህሎት አመራርና ሠራተኞች በየካ ክፍለ ከተማ ሚሊኒየም ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ይገኛሉ፡፡ በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ‹‹ኢትዮጵያ በአለም አደባባይ በተለያዩ አጋጣሚዎች ታላላቅ ታሪኮችን ሰርታለች፡፡ በዛሬው እለት የምናሳርፈው አረንጓዴ አሻራችን እድለኛ በሆነው በእኛ ትውልድ የሚከወን የወርቃማ ታሪካችን አካል ነው›› ብለዋል፡፡ አለማችን በበርካታ የተፈጥሮ አደጋዎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባት ይገኛል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ችግሩ እግራችን ስር ገብቶ ማቃጠል ከመጀመሩ በፊት አሻግሮ ተመልካች በሆኑት መሪያችን አነሳሽነት የአረንጓዴ አሻራ ሥራን የጀመረችው ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራትም እየተረፈች ትገኛለች፤ በዛሬው እለትም ይህንኑ ደማቅ ታሪክ በላቀ ምዕራፍና ደረጃ አሻሽለን የምንደግምበት የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
amAM
Scroll to Top