ስምምቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከቬክና ቴክኖሎጂ እና ከኦርቢት ሄልዝ ጋር በመተባበር ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ ‹‹ብራት ቦክስ›› የተሰኘ ቴክኖሎጂን በሀገር ውስጥ በማምረት በገጠር አካባቢዎች ዲጂታላይዝ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ዓላማ ያለው ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ወደ አምራችነት የሚሸጋግር እና አዳዲስ ዕውቀትንና ክህሎትን ለመታጠቅ ያስችላል፡፡
ይህም በሂደቱ ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ኢትዮጵያ የጀመረችውን ራስን የመቻል ጉዞ ከማሳካት አንፃርም ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
የሥምምነቱ ተግባራዊነት በጤና ቴክሎጂ ምርት፣ በሮቦቲክስና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ብቁ የሰው ኃይል ለማልማት የሚያስችል ዕድልን የሚፈጥር መሆኑም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡