Mols.gov.et

ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የካቲት 3, 2025
ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም የመጀመሪያ ምዕራፍ አፈጻጸምን ገምግሞ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በመድረኩ በመጀመሪያ ምዕራፍ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ለትግበራው የሚያስፈልጉ የሰነድና የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም አደረጃጀትን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ሥራዎች እንደተጠናቀቁ ተጠቁሟል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያው ተቋማዊ ልህቀትን በሚያረጋግጥ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በዚህም የመጀመሪያውን ምዕራፍ በማጠናቀቅ የቀጣዩን ምዕራፍ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መደላድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሪፎርሙ ለውጡን በሚመጥንና ለዜጎች ጊዜውን የዋጀ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተግባራዊ እንደሚደረግም አመላክተዋል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን፣ ተደራሽነትንና ፍትሃዊነትን ለማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቴክኖሎጂ በሰፊው ጥቅም ላይ እንደሚውልም ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና በተጠሪ ተቋማቱ ላይ በሚተገበረው የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ላይ ግልጽነት ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት በየደረጃው ሲካሂድ ቆይቷል፡፡
amAM
Scroll to Top