Mols.gov.et

ማሳሰቢያ

መስከረም 30, 2024
ማሳሰቢያ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እያደረገ ያለው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መነሻና መዳረሻው የዜጎችን መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ በዘርፉ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት በተሰራው ጠንካራ የሪፎርም ሥራ በቴክኖሎጂ ጭምር በመታገዝ ህብረተሰቡን ካላስፈላጊ ወጪና እንግልት በመታደግ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ይህ ሥራ አሁንም ተጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ስምሪቱን በተመለከተ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስምና አርማ እንዲሁም የከፍተኛ አመራሩን ስምና ምስል ጭምር በመጠቀም የተለያዩ ማስታወቂያዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሕገወጦች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሀሰተኛ መሆናቸው ታውቆ ሁሉም ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳይዳረግ ጥንቃቄ እንዲያደረግ እናሳስባለን፡፡ የሥራ ስምሪቱን በተመለከተ አዳዲስ ነገሮች ሲኖሩ የተቋማችንን ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስርን ጨምሮ በሁሉም የሚደያ አማራጮች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ በሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልግ ማንኛው ሰው በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ (https://lmis.gov.et/auth) እንዲመዘገብ እና ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
amAM
Scroll to Top