Mols.gov.et

ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት አመራሩን ማብቃት

ጥቅምት 22, 2023
ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት አመራሩን ማብቃት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በአመራርነት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለካውንስል አባላት በመስጠት ላይ ይገኛል ። ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የአመራሩን ክህሎት ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራትን በቋሚነት እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል ። በየጊዜው የሚሰጡ ስልጠናዎችን ወደ ክልልና ከዚያም በታች ወደሚገኙ መዋቅሮች የማውረድ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር አቶ ንጉሡ በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች በአዲሱ የሚኒስቴር መ/ቤቱ እሳቤ ላይ ያተኮረ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል ። በቀጣይም የዘርፉ አመራሮች በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቀመጡ ዕቅዶችን በስኬታማነት ለመፈጸም የሚያስችል ክህሎትን እንዲላበሱ ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራዎች እንደሚሰሩ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን አብራርተዋል ።
amAM
Scroll to Top