የምንመኛትንና ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትላልቅ ግቦችን ቀርጾ መተግበርን ይጠይቃል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
July 12, 2025
የምንመኛትንና ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትላልቅ ግቦችን ቀርጾ መተግበርን ይጠይቃል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክሀሎት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እያካሄደው የሚገኘው የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የስልጠና መድረክ እንደቀጠለ ነው፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እና ሚኒስቴሩ የክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች ዓመታዊ አፈጻጸም አስመልክቶ ያደረገውን የመስክ ምልከታ ሪፖርት ለውይይት መነሻ በሚሆን መልኩ ቀርቧል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ የዘርፉን ውዝፍ ሥራዎች ሊያካክስ፣ ወቅታዊ ፍላጉትን ሊያሟላ እና የመጪው ጊዜን ታሳቢ ያደረገ አዳዲስ እሳቤዎች በመቅረጽ በየደረጃው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፤ በዚህም ተጨባጭ ውጤቶች መታየት ጀምረዋል፡፡
የተገኙ ውጤቱን በማላቅ የምንመኛትንና ሁለንተናዊ ብልጽግናዋን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ትላልቅ ግቦችን ቀርጾ መተግበርን ይጠይቃል ብለዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከተቋቋመ ጊዜ አንስቶ የዘርፉን ውዝፍ ሥራዎች ሊያካክስ የሚችል ዕቅድ እና አዳዲስ እሳቤዎች በመቅረጽ ሰፋፊ ተግባራት በየደረጃው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ጉልበት ያላቸው ትላልቅ ተግባራት አቅዶ መተግበር እና መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን መጋፈጥም ከዘርፉ አመራር እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡
በተለያዩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የጀመረው ይህ መድረክ የዘርፎችን አፈፃፀም በዝርዝር ለማየት በተናጠል መገምገም ተጀምሯል፡፡ የተናጠል የዘርፎች የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሲጠናቀቅ የጋራ መድረክ የሚኖር ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅና የቀጣይ አቅጣጫዎች ተመላክተው መድረኩ ይጠቃለል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም










