Mols.gov.et

የጥራት ሥራ አመራርን በአግባቡ መተግበር የሪፎረም ሥራዎቻችንን ለማፅናት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ

September 27, 2024
የጥራት ሥራ አመራርን በአግባቡ መተግበር የሪፎረም ሥራዎቻችንን ለማፅናት ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እየተገበረው በሚገኘው ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር የኦዲት ግኝት ላይ ውይይት ተካሄዷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሀ መሀመድ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራርን ለመተግበር የሚያስችሉ ሥራዎች ደረጃ በደረጃ እየተከናወነ ቆይቷል፡፡ ይህን ተከትሎ በሙከራ ደረጃ በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተተገበረ የሚገኘውን ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራርን ውጤታማነትን የሚመዝን የኦዲት ሥራ ተሰርቷል። በኦዲት ግኝቶቹ መሰረት በቀጣይ በአስቸኳይ የማሻሻያና የእርምት እርምጃዎች ተወስደው ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ብለዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሥራዎችን እየተገበረ የሚገኝ ተቋም እንደመሆኑ እነዚህን የሪፎርም ሥራዎች ለማፅናት የጥራት ሥራ አመራርን በአግባቡ መተግበር ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 20 ተቋማትን ዓለም አቀፍ ስታንዳርዶችን እንዲያሟሉ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ቆይቷል፡፡ እስካሁን የጄኔራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እንዲሁም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የISO 9001:2015 እንዲሁም የሀዋሳ ፖሊቴክኒከ ኮሌጅ የISO 21001:2018 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አግኝተዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top