የክህሎት ውድድር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተቋማት ደረጃ መካሄድ ጀመረ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተዋናዮች መካከል ከፍተኛ የውድድር ተነሳሽነትን መንፈስ በመፍጠር በክህሎት ልማት ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ለውጥ የማምጣትና የዘርፉን ገጽታ የመገንባት ዓላማ ያለውን ሀገር ዓቀፍ የክህሎት ውድድር በየሁለት ዓመቱ ያካሄዳል፡፡
ውድድሩ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጀምሮ በየደረጃው የሚካሄድ ሲሆን በመጨረሻም በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄድ ውድድር ፍፃሜውን ያገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከመጋቢት 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ውድድሩ ብሩህ አዕምሮዎች፣ የተፍታቱ እጆችና በክህሎት የበቁ ዜጎች! በሚል ሠሪ ሀሳብ በተቋማት ደረጃ መካሄድ መጀመሩን የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ውድድሩ ሰልጣኞችን፣ አሰልጣኞችንና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን በማሳተፍ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂና በክህሎት ዘርፎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡