የአቃቂ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001: 2015 የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘቱን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡
March 26, 2025

የአቃቂ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001: 2015 የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘቱን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ቢሮው ለኮሌጁ ይፋዊ የማብሰሪያ ስነ-ስርአት በዛሬው ዕለት መካሄዱንም ጠቁሟል፡፡
በማብሰሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝነተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አበራ ብሩ እንደገለጹት፤ የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ ማግኘቱ ኮሌጁ ብቃት ያላቸው ሰልጣኞችን እና ምርቶችን ለገበያው ማቅረብ ያስችለዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መዓዛ አበራ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ በጥራት አመራር ስርዓት ማለፉ ወጥ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋትና ብክነትን በመቀነስ ውጤታማነትን ለመጨመር እንደሚያስችለው ጠቁመዋል፡፡
በከተማዋ ከሚገኙ የመንግስት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የአቃቂ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያገኘ አራተኛው ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የሥራና ክህሎት በዘርፉ ያሉት ተቋማት ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን ያሟሉና የሚሰጡት አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና በሁሉም ደረጃ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
በቅርቡም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጲያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር የትምህርትና ስልጠና ተቋማት (ISO 21001: 2018) እና የባለሙያ ዕውቅና (ISO 17024 :2012) ሥራ አመራር ስርአትን በመተግበር ሂደት የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል፡፡
