Mols.gov.et

የአሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ሥራ እንደሚሰራ ተጠቆመ

September 26, 2024
የአሰልጣኞችን አቅም ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ሥራ እንደሚሰራ ተጠቆመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቸ “ብቃት ለቴክኒክና ሙያ ልህቀት” በሚል የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ አመራሮችና አሰልጣኞች ስልጠና አጠቃላይ ሂደት ገምግመዋል፡፡ በዘርፉ ፖሊሲና አዳዲስ እሳቤዎች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ መፍጠር እና የአሰልጣኞችን ባህሪያዊና ቴክኒካዊ ብቃትን ማሳደግ ታሳቢ ባደረገው በዚህ የስልጠና መድረክ በ19 የስልጠና ማዕከላት ከ20 ሺህ በላይ አሰልጣኞች ተሳትፈዋል፡፡ ይህም ከዕቅዱ 86 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ የሥልጠና መድረኩ ግቡን ያሳካና ለቀጣይ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በርካታ ልምዶች የተገኙበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ እንደ ዘርፍ የተቀረጹ አዳዲስ እሳቤዎችንና ሰትራቴጂዎችን ወደ መሬት ለማውረድ የአሰልጣኞች ሚና የማይተካ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ አሰልጣኞች በፖሊሲና ሰትራቴጂዎች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤና ዝግጁነት እንዲኖራቸው ከማድረጉም ባሻገር በዘርፉ መነቃቃትን መፍጠር ችሏል፡፡ በቀጣይ በተለያዩ ምክንያቶች ስልጠናውን መውሰድ ያልቻሉ አሰልጣኞችን ለመድረስ እንደሚሰራ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር የአሰልጣኞቸ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብሮች ቀጣይነት ባለው መልኩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ለመድረኩ ስኬት አበርክቶ ለነበራቸው አስተባባሪዎች፣ የክልል አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ከፍተኛ የትምህርትና የቴክኒክና ማሰልጠኛ ተቋማት አንዲሁም ለሁሉም ሰልጣኞች ክብርት ሚንስትር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top