Mols.gov.et

የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ የሥልጠና ኮሌጅ 823 ሰልጣኞችን አስመረቀ።

April 14, 2025
የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ የሥልጠና ኮሌጅ 823 ሰልጣኞችን አስመረቀ። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ፤ ኮሌጁ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብር በደረጃ አራት 823 ሰልጣኖችን ያስመረቀ መሆኑን ጠቅሰው ለተመራቂዎችን ለተመራቂ ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በኢንተርፕሪነሪያል እሳቤ የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥና በርካታ የልማት ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ኮሌጅ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ ግብርና ከፍተኛ የሥራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ያመላከቱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተመራቂዎች ግብርናውን በማዘመን የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ እና የአርሶና/አርብቶ አደር ህይወት ለማሻሻል ሚናቸው የማይተካ መሆኑን ጠቁመዋል። ተቋማት የሚመሰርቱት ኢንተርፕራይዝ ሠልጣኞች በኮሌጅ ቆይታቸው በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ገልጸው ሰልጣኞች በስልጠና ማጠናቀቂያቸው የራሳቸውን ኢንተርፕራይዝ መሰርተው እንዲወጡ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ኮሌጆች ያላቸውን አካባቢያዊ ፀጋን መሠረት አድርገው እንዲደራጁ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የአላጌ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ በእንስሳት እርባታና ጤና አጠባበቅ፣ በሆርቲካልቸር፣ በአነስተኛ መስኖ ልማትና በእርሻ መካናይዜሽን ስልጠና ፕሮግራሞች ቀዳሚና ተመራጭ ተቋም መሆንን ራዕዩ አድርጎ እየሠራ ይገኛል፡፡ ኮሌጁ ከ1996 ዓ . ም ጀምሮ እስከ 2017 ዓ. ም በመደበኛውና በማታው መርሀ ግብር 32 ሺህ 211 ሰልጣኞችን በማስመረቅ ለግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top