Mols.gov.et

የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው፡፡ ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር

August 5, 2024
የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው፡፡ ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት ጋር በዘርፉ ተልዕኮና ሀገራዊ ግቦች ዙሪያ በሆሳዕና ከተማ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በዘርፉ ተልዕኮ፣ ሀገራዊ ግቦች እና ግቦቹን ለማሳካት የአመራሩ ሚና ላይ ያተኮረ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ- መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰው በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጸት፤ ክልሉ በርካታ የልማት ፀጋዎች አሉት፡፡ እነዚህን ፀጋዎች በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ሲሆን የታሰበውን ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የቅንጅት ሥራና ምክክር ወሳኝ ነው ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ከግምት በማስገባት እያከናወነ ያለው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ክቡር ርዕሰ-መስተዳድሩ ለትውልድ የሚተርፍ ሥራ ለመስራት ትክክለኛውን አቅጣጫ በመያዝ ሰርቶ የሚያሰራ አመራር እንደሚያስፈልግ ጨምረው ገልፀዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው፣ የተቀረፁት አዳዲስ እሳቤዎች በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንዱስትሪ ግንኙነት ላይ የነበሩ የተከማቹ ችግሮችን ከመፍታት ባለፈ አንደ ሀገር ያሉብንን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ስብራቶችን መጠገን የሚያስችል አቅም ያላቸው ናቸው። ይህን በአግባቡ ተረድቶ በፍጥነት፣ በጥራትና በብዛት ተግባራዊ የሚያደርግ አመራር ወሳኝ ነው ብለዋል። የካቢኔ አባላቱ በበኩላቸው መድረኩ ዘርፉ ላይ ጥሩ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ጠቅሰው በዘርፉ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ርብርብ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
en_USEN
Scroll to Top