Mols.gov.et

‹‹የሴት ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› ውድድር

October 16, 2024
‹‹የሴት ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› ውድድር ወጣት ሴቶች የሚሳተፉበት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን የፈጠራ ሃሳብ ውድድሩ መስከረም 28ቀን 2017 መጀመሩ ይታወቃል ፡፡ ውድድሩ ወጣት ሴቶች የፈጠራ ዕምቅ አቅማቸውን ተጠቅመው የማህበረሰባቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ማመንጨት የሚያስችላቸውን ዕድል ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ‹‹ስታርታፕ ፋውንደርስ የአይሲቲ ኢኖቬሽን›› በሚል ስያሜ ላለፉት 9 ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ለተወዳዳሪዎቹ የአንተርፕሪነርሺፕ ስልጠና የተሠጠ ሲሆን የመወዳደሪያ ሀሳብና ስራዎቻቸውን ያቀረቡበት የእንዲሁም ልምድና ተሞክሮ ያገኙበት መርሃ ግብሮች ተካሂዷል፡፡ ውድድር በነገው ዕለት ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን የውድድሩ አስር አሸናፊዎች የአንድ መቶ ሺ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
en_USEN
Scroll to Top