Mols.gov.et

የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆመ

October 22, 2024
የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን የሚፈልግ መሆኑ ተጠቆ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ የክልሎች አፈፃፀም ግምገማ ቀጥሎ የሲዳማ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በዚህ ዓመት የሚደረገው የሰልጣኞች ቅበላ በየደረጃው ሰፊ የንቅናቄ ሥራን ይፈልጋል ብለዋል፡፡ ዜጎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከመደበኛ እና አጫጭር ስልጠናው በተጨማሪ በልምድ የተገኘ ሙያ ላይ ግብ አስቀምጦ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top