የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ጋር ተወያዩ
October 23, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ጋር ተወያዩ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ ውይይቱ በትምህርትና ሥልጠናው ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂያዊ ግንኙነትን ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና በትምህርትና ስጠናው ዘርፍ የረዥም ጊዜ ትብብር እንዳላቸው የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር አሁን ላይ በኢትዮጵያ ብቸኛው የቴክኒክና ሙያ ልህቀት ማዕከል ሆኖ እያገለገ ያለው የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት በቻይና መንግስት ድጋፍ የተሰራ መሆኑን አውስተዋል፡፡
የተጀመረው ውይይት ስትራቴጂያዊ አጋርነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ፋይዳው የላቀ መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡
የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ሪፎርም አድንቀው በሁለቱ ሀገራት መካከል በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የነበረውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡
በቀጣዮቹ ዓመታት ዘርፉን በቴክኖሎጂና በሰው ሃይል ማጠናከርና ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዘርፉን ሪፎርም መደገፍ የሚያስችሉ ተጨማሪ አዳዲስ የትብብር መስኮች ተለይተው ወደ ሥራ ይገባሉ ብለዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የቻይና ምክትል ትምህርት ሚኒስትር እና የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ተወካይ ዉ ያን ከውይይቱ በኋላ በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የሚገኘውን የሉባን ወርክሾፕ ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድር ከቲያንጅን ቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ዣንግ ጂንጋንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡