የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የካቢኔ አባላት ጋር ውይይት እያደረጉ ነው፡፡
በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ – መስተዳድር ክቡር አቶ እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝነተዋል፡፡
በመድረኩ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ እንዲስሪ ግንኙነት ዙሪያ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን በማጽናት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስለሚቻልበትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ወይይትይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም