Mols.gov.et

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ…

November 27, 2025
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆው የአፈፃፀም ግምገማ፣ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ምዕራፍ እቅድ ትውውቅ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መድረክ አመራርና ሠራተኛው ለቀጣይ ሥራዎች ያላቸውን የላቀ ቁርጠኝነት ያሳዩበት ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫና ቃለ መሐላ በመፈፀም ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ ላይ የቀጣይ ሥራዎች መመሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የራሱን አዳዲስ እሳቤዎች ቀርፆ በለውጥ አስተሳሰብ መቋቋሙ የመንግስት አስተዳደር ሪፎርምን በተገቢው ደረጃ ለመተግበር መሰረት መጣሉን አስረድተዋል፡፡ አዳዲስ እሳቤዎቹ በክህሎት ልማት ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘታቸውን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር የሪፎርሙ ትግበራው ሀገር የመሥራት ኃላፊነታችንን በብቃት እንድንወጣ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በተሰጠው ትኩረትም ሚኒስቴር መ/ቤቱን የጥራት አመራር (ISO 9001 : 2015) ሰርተፍኬት ባለቤት ማድረግ መቻሉንም ገልፀዋል፡፡ የዜጎችን ፍላጎት በሚመጥን መልኩ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ሰፋፊ ሥራዎች የሚጠብቁ እንደመሆኑ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም መደበኛ ሥራዎችን በተቀላጠፈና በተፋጠነ መንገድ በማሳካት የተገልጋዮችን እርካታ ለማረጋገጥ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ በሪፎርሙ ሂደት ራሳችንን ለማስተማር የነበረን ዝግጁነት የዝግጅት ምዕራፉን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችሎናል ያሉት ክብርት ሚኒስትር የተግባር ምዕራፍ ሥራዎች ግልፅነትንና ባለቤትንትን በሚያጎለብት መልኩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች እንደሚተገበሩ አብራርተዋል፡፡ የሪፎርም ትግበራው ሠራተኞች በሠሩት ልክ ዕውቅና የሚያገኙበት፣ የማትጊያ ሥርዓት የሚተገበርበትና፣ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎች የበለጠ ተጠናክረው የሚቀጥሉበት መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስረድተዋል፡፡ ሪፎረሙን በውጤታማነት መተግበር እንዲቻል ለሠራተኞች የተሰጡ የቅድመ ምዘና ውጤቶችን መሰረት ያደረጉ ሥልጠናዎች በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚሰጡና ጠንካራ የሜንቶርሺፕ ስርዓት እንደሚተገበርም ተገልጿል፡፡ የጥራት ሥራ አመራር ስርዓት ትግበራውን በውጤታማነት ማስቀጠል፣ ችግር ፈቺና መፍትሔ አመንጪ ሃሳቦችን በማፍለቅ ቀልጣፋና ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት ለመተግበር በሚኒስቴር መ/ቤቱ የተቋቋመውን (public service innovation lab) የማጠናከር ሥራ በትኩረት እንደሚሠራም አሳውቀዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top