“ዓለም-አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው” ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ
March 14, 2025

“ዓለም-አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው”
ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር ISO 21001/2018 ለመተግበርና የሙያ ብቃት ምዘና እና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በመታገዝ አውቶሜት ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከላትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከዚህ አንፃር ባለፉት ሁለት አመታት ሚኒስቴር መ/ቤቱ ጨምሮ የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ለመተግበር በተከናወኑ ተግባራት የሚታዩ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።
በዚሁ መነሻነት ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችሉ ተቋማት እንደሚገኙ የተናገሩት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ሌሎች አዳዲስ ተቋማት ከቀድሞዎች ልምድ በመውሰድ ራሳቸውን የማዘመን ሥራ ውስጥ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመፍጠር የመድረኩ መዘጋጀቱን አስተውቀዋል።
የሥልጠና እና የምዘና ሥርዓቱን ለማዘመን የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ አውቶሜት የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ጠቁመው የጥራት ሥራ አመራር ስርዓቱን በሚጠበቀው ደረጃ ለመተግበር ተቋማት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑም አሳስበዋል፡፡








