Mols.gov.et

ከውድድር ወደ ምርት…

February 3, 2025
ከውድድር ወደ ምርት… የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተግባራዊ እያደረጋቸው ከሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች መካከል አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ ችግር ፈቺ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎቻቸውን በማበልፀግ ለገበያ ማብቃት አንዱ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት በ2016 በጀት ዓመት‹‹ሰመር ካምፕ›› በሚል ፕሮግራም ከመላ ሀገሪቱ የተወጣጡ ከ400 በላይ ተሳታፊዎች በማሰባሰብ ከ83 በላይ የውጭ ምርትን የሚተኩና አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎች ማምረት ተችሏል። ከእነዚህ ቴክኖሎጂዎች መካከል ዮናስና ጓደኞቹ የሰሩት ጭስ አልባ በሆነ መንገድ ከሠል የሚያከስል እና የእጽዋት መኖ ማቀነባበር የሚችል ቴክኖሎጂ ይገኝበታል። ቴክኖሎጂው “Sumi-automated Charcoal and Animal Feed Production Machine” የማል ስያሜ ተሰጥቶታል። ይህ ቴክኖሎጂ በአገራችን ቆላማ አካባቢዎች ተስፋፍቶ የከርሰ ምድርን ውሃ የሚያጠፋውንና እና የእርሻ መሬትን የሚጎዳውን በሳይንሳዊ ስያሜው Prosopis Juli Flora weed በመባል የሚታወቀውን አረምን በግብዓትነት ይጠቀማል። ከተለያየ የአገራችን አካባቢ የተሰባሰቡት ወጣት ዮናስ እና ሌሎች የሠመርካምፕ ቴክኖሎጂስቶች አልፋ ኢንጂነሪንግን የሚል ኩባንያ መስርተው ቴክኖሎጂውን በብዛት በማምረት ላይ የሚገኙ ሲሆን የቴክኖሎጂውን ፋይዳ የተረዳው የኢፌዲሪ መስኖና ቆላ አካባቢ ሚኒስቴር ቴክኖሎጂው በስፋት እንዲመረት እያደረገ ይገኛል። ይህ አረም ከአገራችን አልፎ የበርካታ የአፍሪካ አገራት ችግር በመሆኑ ቴክኖሎጂውን በቀጣይ ወደተለያዩ አገራት አምርተው የመሸጥ ፍላጎት እንዳላቸውም የቴክኖሎጂው ባለቤቶች ገልጸዋል።
en_USEN
Scroll to Top