Mols.gov.et

ከሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን፡፡

August 13, 2024
ከሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንሠራለን፡፡ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ከሳውዲ አረቢያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ላይ በርካታ ዜጎችን ለማሰማራት የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን የጠቀሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በቀጣይም አሰራሩን ለማሻሻልና ዜጎችን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሠራ አመላክተዋል፡፡ የልዑካን ቡድን አባላቱ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሚሰማሩ ዜጎች የጤና ምርመራ ከሚያደርጉ ተቋማትና የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ኤጀንሲዎች ጋር በሂደቱ የሚታዩ ችግሮችን ለማፍታት የሚያስችሉ ውይይቶችንም አካሄደዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top