ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማላቅ ይገባል። ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
January 29, 2025

ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማላቅ ይገባል።
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለችግር ተጋልጠው የነበሩ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ አፈፃፀምን ገምግሟል።
በመድረኩ የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ ክልሎችና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተገኝተዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢንተርፕራይዞች የማክሮ ኢኮኖሚው ትልቅ ፈተና የሆነውን የሥራ አጥነት ምጣኔን ከመቀነስ አኳያ ሚናቸው የማይተካ ነው ብለዋል።
ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነም አመላክተዋል።
ስለሆነም ሚኒስቴሩ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ፣ ክትትልና ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።
ባለፉት ጊዜያት ከተለያዩ አጋር አካላት በተገኘ ድጋፍ በተመረጡ ክልሎቸ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለችግሮች የተጋለጡ 2350 የሚሆኑ ኢ-መደበኛና መደበኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ተደርጓልም ብለዋል።
ከድጋፉ ሥራ ጎን ለጎን በአማራና ሶማሌ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆኑትን ወደ መደበኛ ሥርዓት የማምጣት ሥራ ተሠርቷል። ተጨባጭ ውጤትም ተገኝቶበታል ብለዋል።
ከዚህ ሥራ የተገኘውን ልምድ እንደ እርሾ በመጠቀም ክልሎች ኢመደበኛ ቢዝነሶችን ወደ መደበኛ ሥርዓት እንዲገቡ በማድረግና በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ከሥራ የወጡትን ኢንተርፕራይዞችን ደግፎ ወደ ሥራ በማስገበት ኢንተርፕራይዞች ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማላቅ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በዘርፉ የቀውስ ጊዜ ሀገራዊ አቅም ለመፍጠር እየተሠራ እንደሆነም ነው ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው ያመላክተዋል።










