Mols.gov.et

ኢትዮጵያ በዓለም አውትሶርሲንግ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

August 20, 2024
ኢትዮጵያ በዓለም አውትሶርሲንግ ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አውትሶርሲን ማህበር እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ኘሮግራም ጋር በጋራ ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ቢዝነስ ኘሮሰስ አውትሶርሲንግ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዜጎች ከሀገራቸው ሳይወጡ በትልልቅ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ አውትሶርስ በተደረጉ ሥራዎች ላይ እንዲሰማሩ ለማስቻል የባለድርሻ አካላት ውጤታማ ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። ከዘርፉ ሀገራችን እንድትጠቀምና ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥር የተጀመሩ የዲጅታል ክፍያ ስትራቴጂና የስታርት አኘ አዋጅ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በየትምህርት ተቋማቱ ተመርቀው የሚወጡ ወጣቶች ለዘርፉ ሰኬት መጠቀም ይገባል ብለዋል። ለዘርፉ ስኬት ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ፣ አይሲቲ ፓርክ፣ የኢንተርኔት መሠረት ልማት የመሳሰሉ ተግባራት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል። ዘርፉ በትኩረት ከተሰራበት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር ለሀገር የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ መሆኑን ተገልጿል። በፍረንጆቹ 2023 የዓለም አቀፍ አውትሶርሲንግ ኢንዱስትሪ ወደ 245 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አስመዝግቧል፣ በ2030 ወደ 525 ቢሊዮን ዶላር ሊያድግ እንደሚችል ትንበያዎች ያሳያሉ። በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረገው 5 ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ደግሞ ለዚህ ዘርፍ ተጨማሪ አቅም የሚፈጥርና እና ብቁና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማቅረብ ያግዛልም ተብሏል ።
en_USEN
Scroll to Top