Mols.gov.et

ኢትዮጵያና ኢራን በክህሎት ልማቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

July 20, 2024
ኢትዮጵያና ኢራን በክህሎት ልማቱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ክቡር አሊ አክባር ረዛኢ ጋር በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በውይይቱ በትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ የአቅም ግንባታ፣ የክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግርን ጨምሮ ኢራን በዘርፉ ያላትን የካበት ልምድና ተሞክሮ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗ ተመላክቷል፡፡ ይህ ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እና የሀገራቱን ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነም በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል፡
en_USEN
Scroll to Top