Mols.gov.et

በምዘና ብቃታቸው ለተረረጋገጠ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ

July 26, 2024
በምዘና ብቃታቸው ለተረረጋገጠ ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጠ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር (GIZ) ጋር በጋራ ሲተገብረው በቆየውን STEP (Sustainable Training and Education Program) ፕሮግራም አፈፃፀም አስመልክቶ ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር) ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ፕሮግራሙ ለቴክኒክና ሙያ ምሩቃን በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ በዕለቱ ክህሎትና ብቃት ያላቸው ሰልጣኞችን ከማፍራት፣ የትብብር ሥልጠናዎችን ከመስጠት ፣ ዲጂታላይዜሽን ከማሳደግ አንፃር በፕሮግራሙ በተከናወኑ ተግባራትና በተገኙ ውጤቶች ላይ ውይይ ተደርጓል፡፡ የመንግሰትና የግሉ ዘርፍ በትብብር ለሚሰጡት ተግባር ተኮር የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች በመንግስት በኩል ከፍተኛ ትኩረት እንደተሰጠውም በውይይቱ ተመላክቷል፡፡ ከውይይቱ ጎን ለጎን የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ምርታቸውን ለዕይታ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን የተዘጋጀ ሲሆን በኮንስትራክሽንና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ላይ ለበርካታ ዓመታት በልምድ ሲሰሩ ለነበሩና ከግል ዘርፍ ጋር በመተባበር በምዘና ብቃታቸውን ላረጋገጡ በቀለም ቅብ፣ በአናጺነት፣ በግንባታ፣ በለሳኝነት ሙያ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የዕውቅና ሰርትፍኬት ተሰጥቷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top