Mols.gov.et

አይሶ 9001፡2015- ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት ለተላበሰ አገልግሎት

August 19, 2024
አይሶ 9001፡2015- ፈጣን፣ ቀልጣፋና ግልጽነት ለተላበሰ አገልግሎት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአይሶ ትግበራ ኮሚቴ አባላት ካሳንቺስ የሚገኘውን የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት የጥራት ሥራ ዓመራር አይሶ 9001፡2015 አተገባበር ምልከታ አደረጉ፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ የተመራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ የጥራት ሥራ አመራር አስተግባሪ ቡድን በካዛንቺስ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተገኝቶ የ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ያለበትን ደረጃ በየሥራ ክፍሎች ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። ዘርፉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተገልጋዮች የሚስተናገዱበት እንደመሆኑ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካት የ ISO የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት የተቀመጡ ስታንደርዶችን በመተግበር ፈጣንና ቀልጣፋ፣ ግልጽነት የተላበሰ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተገልጿል። በተለይ አገልግሎቱን ለማዘመን የተጀመረው ( የወረቀት አልባ ሥራ፣ የአውቶሜሽን፣ የኦን ላይን ምዝገባ፣ የሰነዶች ስርጭትና ዶኩመንቴሽን) የዲጂታይዜሽን ሥርዓት በ ISO የጥራት ስታንደርደ መሰረት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ መሐመድ አሳስበዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አሰራሩን በ ISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት መሰረት ለመምራት እና የአሰራር ወጥነት እና የሥራ ቅልጥፍና ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለለት አይሶ 9001፡2015 በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን በየደረጃው በሚገኙ ተቋማት ተግባራዊ ለማድረግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአሁን ወቅት የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ታግዞ እየተሰጠ ቢገኝም የሚሰጡ አገልግሎቶች በአይሶ ስታንዳርድ እንዲፈጸሙ ማድረግ ይበልጥ ውጤታማነቱን ያሳድገዋል ተብሏል፡፡
en_USEN
Scroll to Top