Mols.gov.et

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ አመታዊ የክህሎት ፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባር ጥናትና ምርምር ዉድድር ተጠናቀቀ።

April 4, 2025
በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረዉ አመታዊ የክህሎት ፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባር ጥናትና ምርምር ዉድድር ተጠናቀቀ። ዉድድሩም በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝ ፣በአንቀሳቃሽ ኢንተርፕራይዞች መካከል በተለያዩ ዘርፎች ላይ እርስ በእርስ ልምድ የተወሰደበት ዉጤታማ ዉድድር እንደነበረም ተጠቁሟል። የወልቂጤ ፖሊ ተክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሀይሩ አህመዲን እንዳሉት በወልቂጤ ክላስተር ኮሌጆች አመታዊ የክህሎት ፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባር የጥናትና ምርምር በተካሄዱ ዉድድሮች መነሻ የሚያደርጉት በእያንዳንዱ ተቋማት ዉስጥ በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝ ፣በአንቀሳቃሽ ኢንተርፕራይዞች መካከል በተለያዩ ዘርፎች ላይ እርስ በእርስ የሚወዳደሩበት ዉድድር እንደሆነም አመላክተዋል። በዚህ አመትም የክህሎት ልማቱ ያለበት ደረጃ ለማየት ፣ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ተመርተዉ ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆናቸዉ የሚገመገምበት እንዲሁም ተቋማቶች ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ ለመፈተሽ የሚደረግ ዉድድር እንደሆነም ተናግረዋል። በክህሎት ፣ በቴክኖሎጂ እና በጥናትና ምርምር ዉድድሮች ሰልጣኝ ከሰልጣኝ ፣አሰልጣኝ ከአሰልጣኝ ፣ኢንተርፕራይዝ ከኢንተርፕራይዝ እንዲሁም ተቋም ከተቋም እየተወዳደሩ የሚፈተሽበት ዉድድር እንደሆነም አስታዉቀዋል። በወልቂጤ ክላስተር ደረጃ 9 ኮሌጆች ፣ 25 ሰልጣኞች ፣ 47 አሰልጣኞች በክህሎት ዉድድር የተሳተፉበት ከ7 በላይ ኢንተርፕራይዞች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተወዳደሩበትና እንዲሁም ከ20 በላይ ቴክኖሎጂዎች ቀርበዉ ዉድድር የተካሄደበት እንደነበረም ተገልጿል። በቀጣይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ በሚዘጋጀዉ ዉድድር ላይ ክላስተሩን ወክለዉ የሚወዳደሩ ሰልጣኞች አሰልጣኞች ፣ኢንተርፕራይዞች የተለየበት እንደሆነም ተነግሯል። በዚህ ዉድድር አንዱ ተቋሙ ከሌላዉ ተቋም ልምድ የወሰደበት እንዲሁም ከባድ የሚመስሉ ስራዎችን እንዴት በጋራ መስራት እንደምንችል የታየበት መሆኑንም ተጠቁሟል።
en_USEN
Scroll to Top